ለመስመር ላይ የፍቅር ጓደኝነት ጠቃሚ ምክሮች

በእያንዳንዱ አመት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ድረገጻችንን በመጠቀም የፍቅር ጓደኛውን/አጋራቸውን ያገኛሉ እንዲሁም ከስጋት ነጻ የመቀጣጠሪያ ልምድ ያገኛሉ። የሚያገኙት ተሞክሮ አስተማማኝና የሚያበረታታ መሆኑን ለማረጋገጥ እባክዎ የመቀጣጠሪያ ደህንነት ፍንጮቻችንን እና የማህበረሰብ መመሪያዎቻችንን ጊዜ ወስደው ያንብቡ።

በመጀመር ላይ

ድህረ ገጻችን የመገኛ አድራሻዎን ለመስጠት ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ በሌሎች ተጠቃሚዎች ማንነትዎ ሳይታወቅ እንዲቆዩ ያደርግዎታል።

የግል የመገኛ አድራሻዎን በተለይም የስልክ ቁጥርዎን፣ ኢሜይልዎን፣ የቤት አድራሻዎን ወይም የአያት ስምዎን በገጽታዎ ላይ በፍጹም እንዳያካትቱ።

የመገኛ አድራሻዎን የሚያምኑት ለመሰልዎት ሰው ብቻ ይስጡ።

ለመስመር ላይ የፍቅር ጓደኝነት ብቻ የሚጠቀሙበትን የኢሜይል አካውንት ያዘጋጁ። ይህም ያልተፈለጉ መልእክቶችን በቀላሉ መለየት እንዲችሉ ያደርግዎታል።

የይለፍ ቃሎችዎን በሚስጥር ይጠብቁ እንዲሁም ለመገመት ቀላል እንዳልሆኑ ያረጋግጡ። ሌላ ቦታ የማይጠቀሙበትን ለመስመር ላይ የፍቅር ጓደኝነት ብቻ የሚሆን ልዩ የይለፍ ቃል ይምረጡ።

ችግሮችን መከላከል

ከአንድ ሰው ጋር በሚነጋገሩበት ወቅት በርካታ ጥያቄወችን በመጠየቅ የሚጋጩ ምላሾችን ወይም የገንዘብ ጥያቄወችን እንዳሉ ልብ ይበሉ።

አንድ ሰው ላይ ጥርጣሬ ካደረብዎት ወይም አንድ ሰው ገንዘብ ከጠየቅዎት፣ በአባሉ ገጽታ ላይ የሚገኘውን የ "ሪፖርት በደል" ምልክትን ወይም የመስመር ላይ ድጋፍ መጠየቂያ ፎርምን በመጠቀም ሁኔታውን ለኛ ሪፖርት ያድርጉልን።

የአባሎቻችንን ማንነት ወይም በገጽታቸው ላይ የሚያስገቡትን መረጃዎች አናረጋግጥም። ምንም እንኳን ተጠርጣሪ አባላትን ለማስወገድ እርምጃዎችን የምንወስድ ቢሆንም፣ ሁሉም አባላት ከሌሎች አባላት ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት እውነተኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ 100% እርግጠኛ መሆን አይቻልም። ከሌሎች አባላት ጋር በሚነጋገሩበት ጊዜ ንቁና ጠንቃቃና ይሁኑ።

በመስመር ላይ ብቻ ለተዋወቁት በእካል ለማያውቁት ማንኛውም ሰው ገንዘብ በፍጹም እንዳይልኩ

ከማግኘቶ በፊት

እያነጋገሯቸው ያሉትን ሰው በአካል ከማግኘትዎ በፊት የቻሉትን ያህል ስለ እኚህ ሰው ለማወቅ ይሞክሩ። ከእኚህ ሰው ጋር በስልክ ከመገናኘትዎ በፊት ኢሜይልን፣ የፈጣን መልእክትን እና ቻትን በመጠቀም በሰፊው ይወያዩ። መስጠት እንደሚፈልጉ እርግጠኛ እስኪሆኑ ድረስ የስልክ ቁጥርዎን ወይም የግል የመገኛ አድራሻዎን አይገልጹ።

እያነጋገሯቸው ያሉትን ሰው በርካታ ፎቶወቻቸውን እንዲልኩልዎ ለመጠየቅ ይሞክሩ። የእኚህን ሰው በተለያዩ ጊዜያት፣ በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ሆነው የተነሷቸውን ፎቶወች ለማየት እንደሚፈልጉ ይንገሯቸው። ይህ እኚህን ሰው በአእምሮዎ ለመሳልና ስለእሳቸው የበለጠ ለመረዳት ይጠቅምዎታል።

በአካል ለመገናኘት ሲወስኑ፣ ሰወች የሚገኙበትን ቦታ ይምረጡ እንዲሁም የት እንደሚሄዱ ለአንድ ጓደኛዎ ይንገሩ።

ከቀጠሮዎ የሚመለሱበትን ሰአትም ያሳውቋቸው።

በመጠናናት ጊዜ

እኚህን ሰው ጊዜ ወስደው ለማወቅ ይሞክሩ። እንደራስዎ ፍጥነት በአንድ ጊዜ አንድ እርምጃ ወደፊት ይጓዙ።

እየተጠናኑ ያሉት ውጭ አገር ካለ ሰው ጋር ከሆነ የባህል ልዩነቶችን ያስተውሉና ጊዜ ወስደው ባህሉን ለመማር ይሞክሩ እንዲሁም እኚህ ሰው ከግንኙነታቹ ምን እንደሚጠብቁ ለመረዳት ይሞክሩ። ከእኚህ ሰው ጋር የቻሉትን ያህል አብረው በማሳለፍ ስለእሳቸው ለማወቅ ይሞክሩ፤ በኢሜይል እና በፈጣን መልእክት ብቻ ተማምነው አይቀመጡ።

ነገሮች ሲርየስ ከመሆናቸው በፊት እኚህን ነው ለማወቅ ተጨማሪ ጊዜ ማጥፋትዎ የከፋ ስህተት ከመፈጸም ይጠብቅዎታል።

ቀለበት ከማሰርዎ በፊት

በየአመቱ በመቶወች የሚቆጠሩ ሰወች በድህረ ገጻችን ላይ የትዳር ጓደኛቸውን ተዋውቀው ደስታና ፍቅር የሞላበት ህይወት አብረው ይኖራሉ። ቀለበት ከማሰርዎ በፊት ምን ችግር ሊፈጠር እንደሚችል ጊዜ ወስደው ያስቡ፤ መብቶችዎንም ይወቁ።

ትዳር መመስረት በህይወትዎ ትልቅ ቦታ ሊሰጧቸው ከሚገቡ ውሳኔዎች መካከል አንዱ በመሆኑ በችኮላ ሊወስኑት አይገባም።

ቀለበት ከማሰርዎ በፊት ስለ የወደፊት የትዳር አጋርዎ በተቻልዎት መጠን የቻሉትን ያህል ማወቅዎን እርግጠኛ ይሁኑ።

የአጋርዎን ጓደኞች እና ቤተሰቦች ይተዋወቁ፦ በአንዳንድ አገሮች ባህል መሰረት አንድን ሰው ሲያገቡ ቤተሰባቸውንም ጭምር ነው የሚያገቡት።

ከሌላ አገር ሰው ጋር ቀለበት ሊያስሩ ከሆነ በዛ ሰው አገር ውስጥ የቤት ውስጥ ጥቃት፣ በደል እና ፍቺ ቢያጋጥምዎ ስለሚኖርዎት መብቶች ተጨማሪ እርምጃዎችን በመውሰድ በደንብ ይረዱ። ብዙ አገሮች አሜሪካን፣ አውስትራሊያን እና የመሳሰሉትን ጨምሮ፣ እድል ሳይቀናቸው ቀርቶ ከሚበድል ወይም ከሀይለኛ ሰው ጋር ትዳር የመሰረቱ ወይም ቀለበት ያሰሩ የውጭ አገር ሴቶችን የቪዛ ሁኔታ የሚጠብቁ ህጎች አሏቸው። ይህም ማለት የቤት ውስጥ ጥቃትን የመሳሰሉ ችግሮች ሲያጋጥምዎ በዛ አገር ውስጥ የመቆየት ህጋዊ መብትዎ እንደተጠበቀ ሆኖ እርዳታ መጠየቅ ይችላሉ።

ፍቺ በሚያጋጥም ወቅት እንደ ዩኤስኤ፣ ዩኬ፣ አውስትራሊያና የመሳሰሉ ብዙ አገሮች የሚገኙ ፍርድ ቤቶች የተለያዩ ሁኔታወችን መሰረት በማድረግ ሁሉም የጋብቻ ንብረቶች ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንዲከፋፈሉ ያደርጋሉ። ስለዚህ ፍቺ በሚያጋጥምዎ ወቅት ምን አይነት ተጽእኖ ሊያሳድርብዎት እንደሚችል ማሰብ ይኖርብዎታል።

ለተጨማሪ የፍቅር ጓደኝነት ደህንነት መረጃ እባክዎ የሚከተለውን ጣቢያ ይጎብኙ:

በኦንላይን ከተቃራኒ ጾታ ጋር በሚደረግ መስተጋብር የደህንነት ምክሮች